
የመጀመሪያ ሳምንት፣ 2ኛ ቀን!
የመጀመሪያ ሳምንት፣ 2ኛ ቀን ቀጣይነት ያለው የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ የልብ ለልብ ግንኙነት እና የግል ድጋፍ አገልግሎት ለለውጥ ስልጠና ቀጥሏል!
አዲስ አበባ፣ የካቲት 17/2018 ዓ.ም
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳሻው ተገኘ ቀደም ሲል ከፈጻሚዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መሠረት ለሁሉም አመራሮችና ፈጻሚዎች “የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ ስልጠና፤ የልብ ለልብ ግንኙነት እና የግል ድጋፍ አገልግሎት ለለውጥ”በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ሥልጠና በሁለተኛው ቀን ቀጥሏል።
የመጀመሪያው ሳምንት ሥልጠና ስለ ማንነት፣ ሁለተኛው ሳምንት የባለቤትነት ስሜት አስተሳሰብ፣ ሦስተኛው ሳምንት ተጠያቂነት እና አራተኛው ሳምንት ደግሞ ኃላፊነት ላይ ያተኩራል።
በዚህ መሰረት የመጀመሪያው ሳምንት 2ኛው ቀን ሥልጠና ማንነት በሚለው ርዕስ ሥር ስለ ዘላቂ የለውጥ ራዕይ ግንዛቤ የተሰጠበት ነበር።
የራዕይ ትርጉም ግለሰብን፣ ማኅበረሰብንና አገርን በማበልጸግ ውስጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው የገለጹት አቶ እንዳሻው ተገኘ የማኅበሩ ራዕይም ለሥራ ፈጣሪ ወጣቶች የመነሻ ካፒታልና ለንግድ ሥራ ማስፋፊያ የሚውል ፋይናንስ አቅርቦ ሕልማቸውንና ተስፋቸውን በማሳካት የበለጸገ ማኅበረሰብን ማየት መሆኑን አንስተዋል።
የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገትና የገበያ ዋጋ ንረትን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው የገለጹት አቶ እንዳሻው በወጣቶች ላይ ትኩረት ማድረጋችንም ለዚሁ ነው ብለዋል። ወጣቶች የአንድ አገር አምራች ኃይል መሆናቸውን በመጥቀስም የማኅበራችን ራዕይ ለወጣቶች ትልቅ ትኩረት በመስጠትና አቅማቸውን በመገንባት የራሳቸው የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው ብለዋል።
በራሳቸው ተነሳሽነት ይህንን ሥልጠና ያዘጋጁት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሥልጠናው ምቹ የሥራ አካባቢን መፍጠርና የአባላትን ችግር የሚፈታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ለእያንዳንዱ ሰው የግል ሕይወትም በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁላችንም 100% የባለቤትነት ስሜት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በመላበስ የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን ያሉት አቶ እንዳሻው ፈጻሚዎች ሥልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉም አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የማኅበሩ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ዓለምጸሐይ ታዙ በበኩላቸው እንዲህ ዓይነት ሥልጠና መዘጋጀቱ የፈረምነውን የቃል ኪዳን ሰነድ በትክክል ወደ ሥራ ለመተርጎም መሠረት ነው ብለዋል። የደንበኞች አገልግሎት ክፍል ኃላፊዋ ወይዘሮ የውብዳር ተክሉ ደግሞ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለአባላት ዘላቂ መፍትሔ ለመሆን የበለጠ ያነሳሳናል ብለዋል።
እንደ ማኅበር የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ መኖሩ ልዩ ያደርገናል ያሉት የማኅበሩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ተሾመ በቀለ በበኩላቸው አርኪ አገልግሎት ለመስጠት ከምንጊዜውም በላይ እንሠራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። የአባላትን ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት መነሳት አለብን ያሉት የማኅበሩ የኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር የኋላሸት ደመቀ ሲሆኑ የአባላትን ወገንተኝነት በመላበስ የማኅበሩን ራዕይ እውን ማድረግ አለብን ሲሉ አክለዋል።
በመጨረሻም የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳሻው ተገኘ ሁሉንም አመራሮችና ፈጻሚዎች አመስግነው የመጀመሪያው ሳምንት 2ኛ ቀን ሥልጠና ተጠናቋል።
ለተጨማሪ መረጃ:
Ticktok: tiktok.com/@terit.saccos
You tube: www.youtube.com/@teritmedia
Telegram: t.me/ethioterit21
Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100070815460611
Website: www.ethioterit.com
Email: info@ethioterit.com
Short Code: 9124



