ከእኛ ምን ያገኛሉ
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃ/የ/ተ/መ/የሕ/ስ/ማህበር የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ የቁጠባ አይነቶች በሁለት ከፍሎ ያስቆጥባል
እነኚህም :-
1.መደበኛ ቁጠባ -
መደበኛ ቁጠባ ማለት አባላት በማህበሩ ውስጥ አባል ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ አባላት በስምምነት የወሰኑትን መደበኛ ብር ሳያቆራርጡ በየወሩ የሚቆጥቡት ቁጠባ ነው(በዚህ በሚያስቀምጡት ቁጠባ ዓይነት አባላት ወለድ ያገኛሉ)
2.የፈቃደኝነት ቁጠባ -
የፍላጎት ቁጠባ ማለት ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ አባላት የፈለጉትን ያህል ገንዘብ ለተለያዩ አገልግሎቶት ማህበሩ ጋር አስቀምጠው በፈለጉት ሰዓት እና ጊዜ ማውጣት የሚችሉበት የቁጠባ አይነት ነው፡፡አባላት ከ7.25% - 9% ወለድ ያገኛሉ) የኢትዮ ጥሪት የቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/ኀ/ሥ/ ማህበር የተለያዩ ሰፊ የቁጠባ አይነቶችን ይሰጣል ።
የቤት ቁጠባ
የማህበሩ አባላት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ለቤት ግዢ ፣ ግንባታ እና ዕደሳት አገልግሎት የሚውል የቁጠባ ዓይነት ነው ፡፡
የሰራተኞች ቁጠባ
የሰራተኞች ቁጠባ ማለት ማህበራችን በመንግሥትም ሆነ በግል ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞችን ለማገዝ እና ለማበረታታት በማሰብ የሚያስቆጥበው የቁጠባ ዓይነት ሲሆን በዚህ ቁጠባም የተሸለ ወለድ ይታሰብላቸዋል
የመኪና ቁጠባ
ለተለያዩ ተሽከርካሪ ግዢ አገልግሎት የሚውል የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡
የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ቁጠባ
የወጣት ስራ ፈጣሪዎች ቁጠባ ማለት ማህበራችን ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት በማሰብ የሚያስቆጥበው የቁጠባ ዓይነት ሲሆን በዚህም ቁጠባ ወለድ ይታሰብላቸዋል።
የጊዜ ግደብ ቁጠባ
የጊዜ ገደብ ቁጠባ ማለት በስምምነት ከዚህ እስከዚህ ቀን ተብሎ ከማህበራችን ጋር በስምምነት ብራቸውን አስቀምጠው የሚቆጥቡበት መንገድ ሲሆን የወለድ መጠኑንም በስምምነት የሚታሰብ ይሆናል። ይህ ቁጠባ ከ አንድ ሚሊዮን የሚጀምር ሲሆን የቆይታ ጊዜውም ስድስት ወር እና ከዚያ በላይ ይሆናል።
የዳስፖራ ቁጠባ
የዲያስፖራ ቁጠባ ማለት ዲያስቦራዎች የሚቆጥቡት የቁጠባ ዓይነት ነው።
የልጆች ቁጠባ
የህፃናት ቁጠባ ማለት አባላት 18 ዓመት ላልሞላቸው ልጆቻቸው የሚቆጥቡት የቁጠባ ዓይነት ነው በዚህም ቁጠባ የተሻለ ወለድ ይታሰባል። ህፃናት ወደ ማህበሩ ሲቀላቀሉ የመመዝገቢያ ክፍያ የማይከፍሉ ሲሆን ሼር የመግዛት ግዴታም አይኖርባቸውም ።
የተቋማት ቁጠባ
የተቋማት ቁጠባ ማለት ማህበራችን ለተቋማት ያዘጋጀው የቂጠባ ዓይነት ሲሆን በዚህ ቁጠባም ወለድ የሚታሰብ ይሆናል።
ከወለድ ነፃ/የዱኒያ ቁጠባ
ከወለድ ነፃ ቁጠባ ማለት ማህበራችን የሸሪዓ ህግን በጠበቀ መልኩ ለሙስሊም እህት ወንድሞቻችን ያዘጋጀው የቁጠባ ዓይነት ነው።
Compulsory Saving
All members are required to contribute to the Compulsory Saving. The deposit amount and schedule are determined by SACCO policy, ensuring collective financial strength and sustainability.
የሴቶች ቁጠባ
የሴቶች ቁጠባ ማለት ማህበራችን በተለየ መልኩ ለሴቶች ያዘጋጀው የቁጠባ ዓይነት ሲሆን በዚህ ቁጠባም ከባክ የተሻለ ወለድ ይታሰብላቸዋል ።
Voluntary Saving
This flexible saving allows members to deposit any amount at their convenience, with the option to withdraw funds on demand or at an agreed-upon future date. It’s ideal for short-term goals, emergency funds, or general-purpose savings
