ከእኛ ምን ያገኛሉ
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህ/ስ/ማ ለአባላቱ በአራት ዐይነት ዘርፎች ብድር ይሰጣል።
የአስቸኳይ ጊዜ ብድር
የአስቸኳይ ጊዜ ብድር የምንለው የትኛውም አባል በ15.5% የብድር ወለድ አባሉ የሚጠበቅበትን ካሟላ በኋላ በአጭር ጊዜ ወስዶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሚመልስበት የብድር ዓይነት ነው የዚህም ብድር ጣሪያው እስከ 10 ሚሊዮን ብር ነው።
የአጭር ጊዜ ብድር
የአጭር ጊዜ ብድር የምንለው በአንድ ዓመት ውስጥ የሚመለስ ሲሆን 13.25 -13.5% ወለድ የሚታሰብበት ነው
የመካከለኛ ጊዜ ብድር
የመካከለኛ ጊዜ ብድር የምንለው ከሁለት እስከ ሶስቱ ዓመት የሚመለስ ሲሆን 14.25 - 14.5 ወለድ የሚታሰብበት ነው
የረጅም ጊዜ ብድር
የረጅም ጊዜ ብድር የምንለው ከሶስት ዓመት በላይ በሆነ ጊዜ የሚመለስ ሲሆን 15.25 - 15.5% ወለድ የሚታሰብበት ነው
የብድር አይነቶች
የመኪና ብድር
የመኪና ብድር ማለት ለማንኛውም ዓይነት ተሽከርካሪ ግዢ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን የብድር ጣሪያውም እስከ 5 ሚሊዮን ብር ሲሆን የመመለሻ ጊዜውም እስከ 10 ዓመት ነው።
የቤት ብድር
የቤት ብድር ማለት ለመኖሪያ ቤት ግዢ የሚያገለግል ሲሆን የብድር ጣሪያውም እስከ 10 ሚሊዮን ብር ሲሆን የመመለሻ ጊዜውም እስከ 20 ዓመት ይሆናል።
የግብርና ስራ ብድር
የግብርና ስራ ብድር ማለት ለተለያዩ ለግብርና ስራዎች የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን የብድር ጣሪያው 5 ሚሊዮን ሲሆን የመመለሻ ጊዜውም እስከ 10 ዓመት ይሆናል።
የማህበራዊ ጉዳይ ብድር
ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳይ ማስፈፃሚያዎች (ሠርግ፣ምርቃት፣ልደት..ወዘተ) የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን የብድር ጣሪያውም 5 ሚሊዮን ሲሆን የመመለሻ ጊዜውም እስከ 10 ዓመት ነው።
የደመወዝ ብድር
የደመወዝ ብድር ማለት በደመወዝተኛ የሆን ሰው ዋስ አድርገው የሚሰጥ የብድር ዓይት የብድር ጣሪያውም እስከ 500,000 ሲሆን የመመለሻ ጊዜም እስከ 10 ዓመት ነው።
የብድር አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ብድር ለመበደር አባላት የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለባቸው
-
1
መደበኛ ቁጠባን ሳያቆራርጡ መቆጠብ
-
2
የብድሩን መጠን 25% ያህል የቆጠበ/ች
-
3
የብድር ማመልከቻ በአካል ተገኝተው በፅሁፍ ማቅረብ (ማስገባት)
-
4
ለጠየቁት ብድር ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ
-
5
ተመጣጣኝ ቋሚ የገቢ ምንጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ች/
-
6
ያገባ/ች /ያለገባ/ች የምስክር ወረቀት ማቅረብ
-
7
ተበዳሪውም ሆነ ዋሱ ባለትዳር ከሆነ በአካል ተገኝቶ መፈረም
-
8
የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ
