በኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር 3ኛ ዓመት 8ኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ ውሎ ምን ተከናወነ?

በጉባኤው ውሎ የኢንስፔክሽን ሪፖርት፣ የ2017 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት፣ የማኅበሩ የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት፣ የ2018 ዓ.ም የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የማኅበሩ የምርምርና ጥናት ሪፖርት ሳቢ በሆነ መልኩና የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅን መሠረት ባደረገ መልኩ ቀርቧል።

የማኅበሩን የኢንስፔክሽን ሪፖርት ያቀረቡት ከኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን የኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ ወይዘሮ ናርዶስ ፀጋዬ፤ ማኅበሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ሕግና ደንብን በአግባቡ መሠረት አድርጎ የተመሠረተና አባላቱን እያገለገለ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።

ወይዘሮ ናርዶስ ለማኅበሩ የአገልግሎት አሰጣጥና አሠራር፣ እንዲሁም ሠራተኞች፣ አመራሮችና ሥራ አስፈፃሚዎች ለማኅበሩ ላላቸው ወገንተኝነት ምስጋና አቅርበዋል።

በተጨማሪም የ2017 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት በኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን የኦዲት ባለሙያ በአቶ ተስፋዬ አቦ የቀረበ ሲሆን፣ አቶ ተስፋዬ እያንዳንዱን የኦዲት ሪፖርት ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት አቅርበዋል።

አቶ ተስፋዬ በሪፖርታቸው ማኅበሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስደናቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ካለፉት የማኅበሩ የኦዲት ሪፖርቶች ጋር በማነጻጸር አስረድተዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት አሠራር ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አሠራር የተለየ መሆኑን የገለጹት አቶ ተስፋዬ፤ ይህ ማኅበር በኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ መሠረት እየሠራ መሆኑን በኦዲታችን አረጋግጠናል ብለዋል።

በመጨረሻም የኦዲት ሪፖርቱ በአብላጫ ድምፅ እንዲጸድቅ ተደርጎ፣ የተገኘው ትርፍ ወደ ካፒታል እንዲያድግ በአባላትና በአባላት ተወካዮች ተወስኗል።

Share this post