የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ ስልጠና – ቀን 1

አንደኛ ሳምንት፤ የመጀመሪያ ቀን!

ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት  የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ ስልጠና የልብ ለልብ ግንኙነት እና የግል ድጋፍ አገልግሎት ለለውጥ የመጀመሪያ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ስልጠና ተሰጠ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16/ 2018 ዓ.ም

የኢትዮ ጥሪት የቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንደሻው ተገኘ ከዚህ ቀደም ከፈፃሚዎች ጋር ያደረጉትን ውይይት መሰረት በማድረግ ለሁሉም አመራሮችና ፈፃሚዎች “የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ ስልጠና ”የልብ ለልብ ግንኙነት እና የግል ድጋፍ አገልግሎት ለለውጥ” በሚል ርዕስ ያዘጋጁትን ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምረዋል።

ለዘላቂ ለውጥ የሚሰጠው ይህ ስልጠና ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን በአራት ዋና ዋና ይዘቶች ተከፋፍሎ ለአራት ሳምንታት ይሰጣል። የስልጠናው ይዘትም፦
•  የመጀመሪያው ሳምንት፡ ስለ ማንነት
•  ሁለተኛው ሳምንት፡ ስለ ባለቤትነት ስሜት
•  ሶስተኛው ሳምንት፡ ስለተጠያቂነት
•  አራተኛው ሳምንት፡ ስለ ኃላፊነት ላይ ያተኮሩ ናቸው።

በዚህም መሰረት የአንደኛው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

በራስ ተነሳሽነት ስልጠናውን ያዘጋጁት አቶ እንደሻው ተገኘ እንደገለጹት ስልጠናው ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር ለአባላት ችግር መፍትሄ ለመስጠት ከሚያስችለው አቅም ባለፈ ለእያንዳንዱ ግለሰብ የግል ህይወት ስኬት እጅግ አስፈላጊ ነው።

“የዚህ ማህበር ቤተሰብ በመሆናችንና የዚህ ስልጠና ተሳታፊ በመሆናችን እድለኞች ነን” ያሉት አቶ እንደሻው የስልጠናውን ዋና ዋና ግቦች ሲያብራሩ የማንነት አመለካከትን ማስተካከል፣ 100% የባለቤትነት ስሜት ያለው አእምሮ መፍጠር፣ 100% የኃላፊነትና የተጠያቂነት ባህልን ማዳበር፣ ከፍተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማላበስ፣ የእድገት አስተሳሰብን መገንባት፣ የተቋሙን ራዕይ መሰነቅ፣ ፅናት፣ አዳዲስ ነገሮችን የመማር ፍላጎት እና ውጤት ተኮር ስራዎች ላይ ማተኮር መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሁላችንም 100% የባለቤትነት ስሜት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በመላበስ የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ስልጠናውን በትኩረት መከታተል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በዚህም መሰረት አመራርና ፈፃሚዎች የቃልኪዳን ማረጋገጫ ሰነድ  የፈረሙ ሲሆን የሰነዱም ይዘት “100% የባለቤትነት ስሜትን በመላበስ የተቋሙ አምባሳደር በመሆን በቤተሰባዊ መንፈስ አባላትን አገለግላለሁ፤ ኃላፊነትን በመውሰድ ያለምንም ምክንያት አእምሮዬን ለአዳዲስ ትምህርቶች ዝግጁ በማድረግና ከተጠበቀው በላይ በመስራት አባላትን አገለግላለሁ፤ ተጠያቂነትን በመያዝ የአባላትን ራዕይ ለማሳካት ግልጽና ታማኝ መረጃ እሰጣለሁ፤ በመልካም ስብዕና በትዕግስት ፈጣን አገልግሎት እሰጣለሁ” የሚል ነው።

የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙላቱ በዕደ በበኩላቸው ስልጠናው በወቅቱ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው የአባላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ መቆም እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኮርፖሬት አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር የኋላሸት ደመቀ በበኩላቸው ለአባላት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመሆን በትጋት መነሳትና የአባላትን አገልጋይነት ስሜት በመላበስ የማህበሩን ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም አቶ እንደሻው ሁሉንም አመራሮችና ሰራተኞች አመስግነው “ቀጣይነት ያለው የCEO የጥበብ ምክር ዕለታዊ ስልጠና ”የልብ ለልብ ግንኙነት እና የግል ድጋፍ አገልግሎት ለለውጥ” የመጀመሪያ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ስልጠና ተጠናቋል።

ለተጨማሪ መረጃ:

Ticktok: tiktok.com/@terit.saccos

You tube: www.youtube.com/@teritmedia

Telegram: t.me/ethioterit21

Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100070815460611

Website: www.ethioterit.com

Email: info@ethioterit.com

Short Code: 9124

Share this post