በስኬት የተጠናቀቀው ጉባኤ!

ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ስራ ማህበር የ4ኛ ዓመት 9ኛ ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በስኬት አካሂዷል፡፡

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም

ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የኅብረት ስራ ማህበር ከወጣቶች መረዳጃ ዕድር ተነስቶ በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ በተመሰረተ በ4 ዓመታት ውስጥ ራሱን ወደ ግዙፍ ህዝባዊ የፋይናንስ ተቋምነት ማሳደግ ችሏል፡፡

እስካሁን ያካሄዳቸውን 8 ዙር ጠቅላላ ጉባኤያት በወቅቱ በማካሄድ ግንባር ቀደም የሆነው ማህበሩ በትናንትናው ዕለትም 9ኛ ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ ከማካሄድ በተጨማሪ 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉንም በድምቀት አክብሯል፡፡

የፌዴራል ኅብረት ስራ ማህበር ኮሚሽን ተወካይን ጨምሮ የአባላት ተወካዮችና አባላት፣ የማህበሩ አመራር ኮሚቴዎች፣ ስራ አስፈጻሚዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የዕለቱን ፕሮግራም በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዕዝራ ወ/ሰንበት ሲሆኑ የማህበሩ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ እንዳሻው ተገኘ ደግሞ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ማህበሩ ተዓምራዊ ሲሉ የጠሩትን እድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በተለይ ያለፈው የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በተለያዩ መመዘኛዎችና መለኪያዎች እግጅ ግዙፍ የሆነ እድገት ያስመዘገበበት እንደነበር የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው ለዚህም ከማህበሩ አባላት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የማህበሩ አመራሮችና ፈጻሚ ሰራተኞች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው አመስግነዋል፡፡

የተለያዩ ፕሮግራሞች በተካሄዱበት በዚህ እለት ማህበሩ ተስመርቶ ስራ ላይ ባሳለፈባቸው 4 ዓመታት የመጣባቸው የስኬት መንገዶች ምን እንደሚመስሉ፣ ምን ፈተናዎች አጋጥመውት እንዴት መፍትሄ እንዳበጀላቸው እንዲሁም ያሳካቸውን ስኬቶች እንዴት ማስቀጠል ይቻላል የሚሉትም ተነስተው ነበር፡፡

በተጨማሪም ማህበሩ በ2018 በጀት ዓመት ከሰራቸው ስራዎች መካከል የበጎ አድራጎት ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸው የተነሳ ሲሆን ሌሎች የስራ ክንውኖች ምን መልክ እንደነበራቸው የሚጠቁሙ ሪፖርቶችም ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችና የሚሻሻሉ ህጎች በጉባኤው ላይ ቀርበው የአባላት ተወካዮች ሰፊ ውይይት ካደረጉባቸው በኋላ የተወካዮቹን ይሁንታ አግኝተው ፀድቀዋል፡፡

በመጨረሻም ማህበሩ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ድርጅቶችና ተቋማት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን ማህበሩን በማደራጀት ሂደት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል የተባሉ አካላትም እንዲሁ ተሸልመዋል፡

ለተጨማሪ መረጃ:

Ticktok: tiktok.com/@terit.saccos

You tube: www.youtube.com/@teritmedia

Telegram: t.me/ethioterit21

Facebook: www.facebook.com/profile.php?id=100070815460611

Website: www.ethioterit.com

Email: info@ethioterit.com

Short Code: 9124

Share this post